top of page
Our Work
Since our foundation, Enehogn has been on a mission to create a better world for all. Our accomplishments include building schools and providing educational resources, developing sustainable housing solutions, and offering financial assistance for those children in need. We believe that working together to support those who need it the most is the key to creating lasting change. Check out our PDF containing all of our past works to learn more about the ways we've made a difference and join us in our mission to make the world a better place.
Jun 26, 2020
የእነሆኝ የበጎ አድራጎት ማህበር በአሜሪካና በካናዳ የሚገኙት አባላት የወቅቱን የወረርሸኝ በሸታ ለመከላከል 4150 የአፍ ማፈኛ ማሰክ ትብብር አደረጉ እንደሚከተለው አከፋፍለናል።
1ኛ.ለቆቦ የመጀመሪያ ደረጃ ሆሰፒታል ብዛት 1000 የአፍ ማፈኛ ማሰክ
2ኛ.ለቆቦ ከተማ አሰተዳደር ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት ብዛት 1300 የአፍ ማፈኛ ማሰክ
3ኛ.የራያ ቆቦ ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት ብዛት 1300 የአፍ ማፈኛ ማሰክ
4ኛ.ቀሪውን የአፍ ማፈኛ ማሰክ ለእነሆኝ አባላት ,እነሆኝ ለሚረዳቼው አረጋውያን,ለተረጂ ህጻናት እና ለማህበሩ ደጋፊዎች ያከፋፈልን ሲሆን በዚህም ጊዜ የማህበሩን ጥሪ አክብረው የተገኙት
1ኛ.አቶ ንጉሰ አብርሀ የቆቦ ከተማ አሰተዳደር ምክትል ከንቲባና የቴክኒክና ሙያ ሀላፊ
2ኛ.አቶ ካሳሁን አዲሱ የቆቦ መጀመሪያ ደረጃ ሆሰፒታል ሰራ አሰኪያጂ
3ኛ.አቶ ተፈራ ጥላሁን የራያ ቆቦ ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት ምክትል ሀላፊ
4ኛ.ሲ/ር ከበቡሸ ካሳው የቆቦ ከተማ አሰ/ር ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት ሀላፊ
5ኛ.ወ/ሮ ሀብታም አማረ የራያ ቆቦ ወረዳ ሴቶችና ህጻናት ጽ/ቤት ሀላፊ
6ኛ.የእነሆኝ የበጎ አድራጎት ማህበር የሰራ አመራር ቦርድ እና የጽ/ቤቱ ሰራ አሰኪያጂ በተገኙበት የማሰራጨት ሰራ የሰራን ሲሆን ለዝህም በጎ ተግባር የማህበሩን ጥሪ አክብራችሁ የተገኛችሁ የየጽህፈት ቤቱ ሀላፊውች በማህበሩ ሰም ላቅ ያለ ምሰጋናችንን እናቀርባለን።
Dec 20, 2020
የእነሆኝ የበጎ አድራጎት ማህበር ቦርድ ሰብሳቢ አባ ቀለመወረቅ አስፋዉ ፣የቦርዱ ኦዲተር አብዱ መንገሻ ፣ የማህበሩ ሂሳብ ባለሙያ አቶ ኢዮብ በላይ ፣የማህበሩ ስራ አስኪያጅ አቶ መንገሻ ምስጋን እና ከአሜሪካን ወደ ኢትዮጸጵያ ለዕረፍት የመጣዉ የእነሆኝ አባል አቶ ሲራጅ ሙሃመድ በተገኙበት ቆቦ ሃይስኩል ት/ቤት ግቢ ዉስጥ ቅዳሜ 10/04/2013 ዓ.ም ጧት 4:00 ሰዓት በቆቦ ከተማ አስተዳደር ከተመለመሉት 30 ህፃናት 25 እና በራያ ቆቦ ወረዳ አስተዳደር የተመለመሉትን 30 ህፃናት ለትምህርት የሚሆናቸዉን ደብተር ፣ ድሮዊንግ ደብተር ፣ እስክርቢቶ ፣ እርሳስ ፣ ላጺስ ፣ መቀረጫ እና ቦርሳ ሲሰጡ የሚያሳይ ፎቶ ግራፍ /video ነዉ።
Jun 4, 2021 የእነህኝ የበጎ አድራጎት ማህበር አመራር ቅዳሜ በ21/9/2013 ዓ.ም በሐይቅ ከተማ በጃሪ እና በመካነ ኢየሱስ ግቢ ወስጥ የሚገኙትን ህፅናት በቦታዉ ተገኝቶ በማየት ደስታ እየተስማን ነገር ግን የአኗኗራቸው ሁኔታ ስናይ ደግሞ ውስጣችን እዝነኖል። ይህንን ችግር በማየት እነሆኝ $80,000.00 ብር ለጃሪ ጣቢያ $80,000.00 ብር ለመካነ ኢየሱስ ጣቢያ በአጣቃላይ $160,000.00 ብር ድጋፍ እነሆኝ አድርጉል። ከዚህ በታች VIDEOS የሚታየዉ በሐይቅ ከተማ በጃሪ እና መካነ ኢየሱስ ግቢ የሚገኙት ተፈናቃዮች እና የእነሆኝ አመራር ናቸዉ ።
Jul 9, 2021 እነሆኝ ለቆቦ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ለኮቪድ አገልግሎት የተመረጠና እየሰጠ የነበር መሆኑ ይታወቃል። የሆስፒታሉ ስራ አስኪያጁም በደብዳቤ ለእነሆኝ የአቆሻሻ ማጠራቀሚያ እና መቆያ ክፊል አለመኖር አብይ ችግራቸዉ ስለሆን በጠየቁን መሰረት እነሆኝ የበጎ አድራጎት ማህበር ማተርያል በማቅረብ እየተከታተለ በማሰራት አጠቃላይ ወጭ $85,049 ብር (ሰማኒያ አምስት ሽህ አርባ ዘጠኝ ብር ወጭ በማድረግ አስርተናል።
January 25, 2022 በሐገራችን በኢትዮጵያ በደረስው የፖለቲካ ጦርነት ትልቅ ችግር ውስጥ ገብተው ስላሉ በቆቦ ወረዳ የአምስቱ ቀበሌዎች ከከንቲባው ፅ/ቤት ደብዳቤ ከተረጆች ስም ዝርዝር ጋር በደርስን ደብዳቤ መስርት 100 ኩንታል ዱቄት በመግዛት ለ400 ቤተስቦች ለያንዳንዱ 25 ኪሎ በእነሆኝ መሪነት ከወረዳው ቀበሌ ስራተኞች ጋር በመተባበር ለቆቦ ወረዳ እርዳታችነን ስጥተናል።
Jan 25, 2022 በቆቦ ወረዳ ሆስፒታል በነበረው ጦርነት ምንም ሕብረተስቡ የሚገለገልበት መድሐኒቶች ባለመኖሩ ቆቦ ከተማ ነፃ ከወጣ ብሖላ ሆስፒታል ባለ ሙያተኞች ለእነሆኝ ባስቸኳይ እርዱን ስላሉን በወቅቱ የሚያስፈልጋቸው የመድሐኒቶች ስም ዝርዝር ተስቶን $57.00 ያወጣ መድሐኒቶች ለሆስፒታሉ እነሆኝ አስረክቦል:: ለሆስፒታሉ የተሰጡ የተለያዩ መድኃኒቶች
October 1, 2022, በነበረው በሐገራችን በኢትዮጵያ ጦርነት ወደ ውርጌሳ ብዙ ህፃናትን የያዙና ለመውለድም በጣም የቀረቡ እናቶች በጣም ትልቅ ችግር ላይ እንዳሉ በቆቦ ወረዳ መንግስት ባለስልጣናት እንሆኝ እንድንረዳ በመጠየቅነው መስረት እኛም በማስተባበር 216 ቤተስብ $300,000.00 ዱቄት በመግዛትና እንዱሁም 100 ህፃናት ለያዙ እናቶች $1000.00 ስጥተናል ::
2022 እነሆኝ ለቆቦ ከተማ 2 ደረጃ ትምህርት ቤት እንድንረዳ በተጠየቅነው የላይብረሪ ቤቱን መፀሐፍትን ማሞላት ነበር በተስጠን የመፀሐፍ ስም ዝርዝር መስረት በመግዛት ለትምህርት ቤቱ አስረክበናል
Jun 25, 2023 ለእነሆኝ ልጃችን ለመዓዛ ሲሳይ ክራንች በዛሬዉ ዕለት እናቷና አያቷ በተገኙበት ማስረከባችነን እየገለፅን ከላይ ተጨማሪ ቪዲዮ ልከናል
bottom of page